በዓለም ዙሪያ ከአስራ ሁለት በሚበልጡ ከተሞች ዛሬ ማክሰኞ ሠላሳ አምስተኛው የቲያናንመን አደባባይ ጭፍጨፋ መታሰቢያ እየተካሄደ ነው፡፡ በቻይና እና በሆንግ ኮንግ ደግሞ ባለስልጣናቱ በሲቪል ማሕበረሰብ ቡድኖች ላይ ብርቱ ቁጥጥር በማድረግ ላይ ናቸው፡፡
ከመታሰቢያው ዕለት ቀደም ብሎ የሆንግ ኮንግ ባለስልጣናት ስምንት ሰዎችን በማሕበራዊ መገናኛቸው ላይ ባወጡት ይዘት ምክንያት አስረዋቸዋል፡፡ ከታሰሩት መካከል ታዋቂው የሰብዓዊ መብት ጠበቃ ቻው ሃንግ ይገኙበታል፡፡ ሃንግ እአአ በ 2021 በሆንግ ኮንግ ቪክቶሪያ ፓርክ የሻማ ማብራት መታሰቢያ በማደራጀታቸው መታሰራቸው ይታወሳል፡፡ ቤጂንግ ከዚያ በቀደመው ዓመት በሆንግ ኮንግ ባጸናችው አወዛጋቢ የጸጥታ ሕግ በስፍራው የቲያናመን አደባባይ ጭፍጨፋ መታሰቢያ እንዳይካሄድም መከልከሏ አይዘነጋም፡፡
በርካታ የቤጂንግ ደጋፊ ድርጅቶች በተከለከለው የሻማ ማብራት መታሰቢያ ምትክ ቪክቶሪያ ፓርክ መናፈሻ የምግብ ድግስ ዝግጅቶች እያካሂዱ ሲሆን አንዳንድ የመብት ተሟጋቾች ምጸት አድርገው ተመልክተውታል፡፡
መድረክ / ፎረም