በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰሜንና የደቡብ ኮርያ ተደራዳሪዎች የመጀመሪያ ንግግር


የሰሜንና የደቡብ ኮርያ ተደራዳሪዎች በዩናይትድ ስቴትስ ከሚመራ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዕዝ ጋር ሆነው ዛሬ የመጀመሪያ ንግግር እያካሄዱ ናቸው።

የሰሜንና የደቡብ ኮርያ ተደራዳሪዎች በዩናይትድ ስቴትስ ከሚመራ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዕዝ ጋር ሆነው ዛሬ የመጀመሪያ ንግግር እያካሄዱ ናቸው። ሁለቱን ኮርያዎችን በሚለየው ከባድ ምሽግ ባለበት ቦታ ውስጥ ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ነፃ በሆነው ቀጠና ነው የተሰበሰቡት።

የሰሜንና የደቡብ ኮርያ መሪዎች ባለፈው ወር ሦስተኛ ስብሰባ ባካሄዱበት ወቅት የጣምራ ፀጥታ ቀጠና የተባለውን እአአ በ1953 የኮርያው ጦርነት ሲያበቃ ሦስቱ ወገኖች ሲቆጣጠሩት የቆየውን ቦታ ከወታደራዊ ይዘት ለማፅዳት ተስማምተዋል። የማፅዳቱ ተግባር እስከ ታኅሣስ ወር ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ እንዲከናወን ይጠበቃል። የተቀበሩ ፈንጂዎችን ማስወገድ፣ የጥበቃ ኬላዎችን ማንሳት፣ የሥለላና ሌሎች ወታደራዊ ዕቃዎችን ማራቅ ያካተተ ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG