ከጥቂት ወራት በፊት የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት በአቶ ኤልያስ ክፍሌ፣ በአቶ ዘርይሁን ገብረእግዚአብሔር፣ በጋዜጠኛ ውብሸት ታየ፣ በወ/ሮ ሂሩት ክፍሌ እና በወ/ት ርዕዮት ዓለሙ ላይ በቀረበባቸው የሽብርተኝነት ክሥ የጥፋተኛነት ብይን ሰጥቶ ከ14 እስከ 19 ዓመታት የሚደርስ የእሥርና የተለያዩ የገንዘብ መቀጫዎችን ጥሎባቸው ነበር፡፡
ከእነዚህ መካከል የብሔራዊ አንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ዘርይሁን ገብርእግዚአብሔር፣ የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ምክትል ዋና አዘጋጅ ውብሸት ታየ እና ወ/ሮ ሂሩት ክፍሌ የተባሉት የቤት እመቤት ይቅርታ መጠየቃቸውን ጠበቃቸው የነበሩት አቶ ደርበው ተመስገን ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል፡፡
ደንበኞቻቸው አንከራከርም በማለታቸውና የይቅርታው ሂደት ተጠቃሚ መሆን በመፈለጋቸው ሥራቸውን ማቋረጣቸውን ጠበቃው ተናግረዋል፡፡
ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ፡፡