በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሲዳማ ከአንድ ቤት ሦስት ህፃናት በቃጠሎ ሞቱ


የኢትዮጵያ ካርታ
የኢትዮጵያ ካርታ

በሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን በንሳ ወረዳ ሞኮንሳ ቀበሌ ውስጥ፣ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በአንድ ቤት ላይ በተነሳ እሳት ሁለት መንታ እህትማማቾች እና አንድ ወንድማቸው መሞታቸውን፣ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የምርመራ ክፍል ሓላፊ ዋና ሳጂን አበራ ሹና ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

በሲዳማ ከአንድ ቤት ሦስት ህፃናት በቃጠሎ ሞቱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:22 0:00

የልጆቹ ወላጆች ለጉዳይ ወጣ ባሉበት በ15 ደቂቃ ውስጥ አደጋው ማጋጠሙን ፖሊስ ገልጾ፣ ሴቶቹ ተቃውጥለው መሞታቸውንና ታላቅ ወንድማቸው በሩ ስር ወድቆ በጭስ ታፍኖ መሞቱን ፖሊስ አስታውቋል። የህፃናቱ አባት አቶ ዲራጎ ብኖራ፣ “የዐሥር ዓምቱ ወንድ ልጄ እና የሴቶቹ ታላቅ አንድ ላይ ቤት ውስጥ ነበሩ። ሁለቱ ሴቶች የሦስት ዓመት መንታዎች ሲኾኑ አንደኛዋን አስተኝቼ፣ አንደኛዋ ከወንድሟ ጋራ እየተጫወተች ነበረ የወጣሁት። ወጥቼ ብዙም አልቆየሁም። ጩኸት ሰምቼ ስመለስ ቤቴ እየተቃጠለ መኾኑን አየሁ፤ ልጆቼን ለማዳን ብሞክርም ላተርፋቸው አልቻልኩም። መዓት ነው የወረደብኝ” ብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG