በጋዜጣው ዘገባ መሠረት የአሜሪካ እስላማዊ ግንኙነት ምክር ቤት የእጅ ፁሑፍ የሆነውና ኮፒ ተደርጎ የተላለፈው ማስጠንቀቂያ ለደረሳቸው ሦስት መስጂዶች፣ ተጨማሪ የፖሊስ ኃይል ጠይቋል።
ደብሳቤው የደረሳቸው ደቡብ ካሊፎርኒያ ውስጥ የሚገኙት ሁለቱ የ'ሎንግ ቢች' እና የ'ካርሊሞንት እስላማዊ ማዕከል' በሚል የሚታወቁት እንዲሁም፣ ሰሜን ካሊፎርኒያ ሳንጆሴ ውስጥ የሚገኘው 'ኤቨርግሪን እስላሚክ ማዕከል'ናቸው።
ደብዳቤዎቹ የተላኩት ለ"ሰይጣን ልጆች" ተብለው ሲሆን፣ የተፈረሙት ደግሞ "አሜሪካንስ ፎር ኤ ቤተር ዌይ" ተብለው መሆኑንም 'ሎስ አንጀለስ ታይምስ' ጋዜጣ ዘግቧል።
Los Angeles Times reported Saturday.