በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ሱዳን ተፈናቃዮች ያለምግብና ውሃ እየተሰቃዩ መሆናቸው ተገለፀ


በደቡብ ሱዳን የዬኢ ክፍለ ግዛት ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት፣ ግጭቶችን ሽሽት ባለፉት ሁለት ሣምንታት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ብዙ ሺህ ነዋሪዎች፣ በአሁኑ ወቅት ያለምግብና ውሃ እየተሰቃዩ ናቸው።

6ሺህ የሚሆኑ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ በአሁኑ ጊዜ የሚኖሩት፣ ከዬኢ ከተማ ውጭ በዛፎች ሥር ነው ሲል - የዬኢ የዕርዳታና መልሶ ማቋቋሚያ ኮሚሽን አስታውቋል። ሌሎች ደግሞ ድንበር ተሻግረው ወደ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ ሄደዋል ብሏል።

የዬኢ ክፍለ ግዛት ነዋሪዎች የሚፈናቀሉት በመንግሥቱ ኃይሎችና በቶማስ ሢሪሎ በብሄራዊ ዓርነት ግንባር ሽምቅ ተዋጊዎች መካከል የሚካሄደው ውጊያ እየተባባሰ በመምጣቱ ነው።

ወታደሮች ሲቪሎችን መግደላቸውን ሴቶች መድፈራቸውንና መላ መንደሮችን ማቃጠላቸውን እማኞች ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ተናግረዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG