በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተቃውሞ ሰልፍ በካርቱም


ሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ውስጥ ሙሉ በሙሉ ሲቪላዊ አስተዳደር እንዲመሰረት የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰልፍ
ሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ውስጥ ሙሉ በሙሉ ሲቪላዊ አስተዳደር እንዲመሰረት የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰልፍ

ሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ውስጥ ሙሉ በሙሉ ሲቪላዊ አስተዳደር እንዲመሰረት የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ።

የነጻነት እና የለውጥ ኃይሎች ተብሎ የሚጠራው ጥምረት ደጋፊዎች ትናንት ሰልፍ የወጡት ባለፈው ቅዳሜ በጦር ሰራዊቱ የሚመራ አስተዳደር ደጋፊዎች ሲቪሉን አስተዳደር በመቃወም ያካሄዱትን ሰልፍ ተከትሎ ነው።

በብዙ ሲዎች የተቆጠሩት አፍካሪ ዲሞክራሲ ሰልፈኞች ባለፈው ቅዳሜ የጦር ሰራዊቱ ደጋፊዎች ለስድስት ቀናት ያለማቋረጥ በተቀመጡበት በቤተ መንግሥቱ ዙሪያ ሰልፋቸውን እንዳካሄዱ ሮይተርስ ዘግቧል።

ተቀናቃኝ አንጃዎች የያዙት ግብግብ እአአ በ2023 ሊካሄድ ከታቀደው ምርጫ አስቀድሞ ደካማውን የሥልጣን ክፍፍል ሥምምነት ያፈርሱት ይሆናል የሚል ሥጋት ተፈጥሯል።

እአአ በ2019 የረጅም ጊዜው አምባገነን ኦመር አል በሽር ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ ሲቪላዊ እና ወታደራዊ መሪዎች በጋራ እያስተዳደሩ ናቸው።

ሆኖም የሽግግሩ መንግሥት ወታደራዊ መሪዎች ሲቪላዊው ካቢኔ እንዲፈርስ መጠየቃቸውን ተከትሎ የዲሞክራሲ ምስረታው ተስፋ እየጨለመ መጥቷል።

ትናንት ሰልፍ ያደረጉት ተቃዋሚዎች ወታደራዊ መሪው ጄኔራል አብደልፋታህ አል ቡርሃንን "አሁንም የአልበሽር ደጋፊነታቸውን ቀጥለዋል" በማለት እንደወነጀሏቸው አልጀዚራ ዘግቧል። የጀነራል ቡርሃን ደጋፊዎች በበኩላቸው የጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ አስተዳደር የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ጉዳት ላይ ጥሎታል በማለት ይከሳሉ።

ውጥረቱ እንደቀጠለ ቢሆንም ጀነራል ቡርሃን እና ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዶክ ደጋፊዎቻቸው ድምጻቸውን በሰላማዊ መንገድ እንዲያሰሙ መጠየቃቸውን ቀጥለዋል።

XS
SM
MD
LG