በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ሕብረት አባል ሃገሮች መሪዎች ጉባዔ በሞሪታኒያ

ሠላሳ ርዕሳነ ብሔራት የተካፈሉበት የአፍሪካ ሕብረት አባል ሃገሮች የመሪዎች ጉባዔ ሞሪታኒያ ዋና ከተማ ኖክሾት ላይ ተከፍቷል። የሁለት ቀናቱ ጉባዔ ዋና ትኩረት ሙስናን መዋጋትና ለአህጉሪቱ የሰብዓዊና እና የፀጥታ ቀውሶች መፍትሄ መፈለግ እንደሚሆን ተጠቁሟል።

ሠላሳ ርዕሳነ ብሔራት የተካፈሉበት የአፍሪካ ሕብረት አባል ሃገሮች የመሪዎች ጉባዔ ሞሪታኒያ ዋና ከተማ ኖክሾት ላይ ተከፍቷል። የሁለት ቀናቱ ጉባዔ ዋና ትኩረት ሙስናን መዋጋትና ለአህጉሪቱ የሰብዓዊና እና የፀጥታ ቀውሶች መፍትሄ መፈለግ እንደሚሆን ተጠቁሟል።

የሞሪታንያ ፕሬዚዳንት መሃመድ ኡልድ አብደል አዚዝ ትናንት ዕሁድ ባደረጉት የመክፈቻ ንጝር ማሊ ውስጥ የፈረንሳይ ወታደሮችን ዒላማ ያደረገውን እኛ አራት ሲቪሎች የተገደሉበትን ጥቃት በመጥቀስ በአህጉሪቱ ሥላሉት የፀጥታ ችግሮች አስጠንንቀዋል።

በፅንፈኞች የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ለመዋጋት በጋራ መንቀሳቀስ ይኖርብናል ሲሉ የሞሪቴንያው ፕሬዚዳንት ጥሪ አቅርበዋል።

አፍሪካ ሙስናን ለመግታት ካልቻለች ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ሊመጣ አይችልም ሲሉም አሳስበዋል።

መሪዎቹ የኢትዮጲኣያና ኤርትራ የሰላም ጥረትና ደቡብ ሱዳንን በሚመለከትም እንደሚወያዩ ተገልጹዋል።

በማሊ ካሜሩን ኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክና ዚምባቡዌ በሚካሄዱት ምርጫዎች ላይም ይነጋጋራሉ ተብሉዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG