በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኃብተሥላሴ ታፈሰ አረፉ


ኃብተሥላሴ ታፈሰ
ኃብተሥላሴ ታፈሰ

ለኢትዮጵያ ቱሪዝም የመሠረት ድንጋይ ያኖሩት ልጅ ኃብተሥላሴ ታፈሰ በ91 ዓመት ዕድሜያቸው ዛሬ አረፉ፡፡

ለኢትዮጵያ ቱሪዝም የመሠረት ድንጋይ ያኖሩት ልጅ ኃብተሥላሴ ታፈሰ በ91 ዓመት ዕድሜያቸው ዛሬ አረፉ፡፡

የኢትዮጵያ ቅርስና ታሪክ ወርሶች በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት - ዩኔስኮ ሰፊ ዕውቅና እንዲያገኝ መሠረት ያኖረ ተግባር የፈፀሙት ኃብተሥላሴ ታፈሰ የጢስ ዓባይ፣ ጣና፣ ጎንደር፣ ላሊበላና አክሱም የጎበኝት መሥመር እንዲዘረጋ፣ እንዲታወቅ ያደረጁ

“የኢትዮጵያ ቱሪዝም አባት” ናቸው፡፡

ባለብዙ ሙያና ባለብዙ አንደበቱ ልጅ ኃብተሥላሴ ታፈሰ ከቱሪዝም ተግባራቸው ሌላ የልዑል መኮንን ኃይለሥላሴ መታሰቢያ የሆነው የዛሬው ጥቁር አንበሣ ሆስፒታል እንዲከፈት ሃሣብ ለንጉሡ አቅርብወና አሳምነው ወደ ተግባር እንዲገባም ያደረጉ ሰው ናቸው፡፡

ልጅ ኃብተሥላሴ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሬስ ኃላፊ ሆነው ሥራ ከመጀመራቸው በፊት በዩናይትድ ስቴትስ በመንግሥት ግንኙነት ጉዳዮች የመጀመሪያ ዲግሪ ሠርተዋል፡፡

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁት በተፈሪ መኮንን አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ነው፡፡

ልጅ ኃብተሥላሴ ታፈሰ ሦስት ልጆችን አፍርተዋል፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG