በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሦስተኛ የዩናይትድ ስቴትስ ድሮን የመን ውስጥ ወደቀ


በእስራኤል ሐማስ ጦርነት ምክንያት ሁቲ ታጣቂዎች በቀይ ባሕር አካባቢ በመርከቦች ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት በቀጠሉበት በአሁኑ ወቅት ሦስተኛ የዩናይትድ ስቴትስ “ኤምኪውሪፐር” ሰው አልባ አውሮፕላን የመን ውስጥ መውደቁ ተገለጠ፡፡

ሁቲዎቹ ታጣቂዎች በየመን በረሐማው ማሪብ ክፍለ ግዛት ድሮኑ ከየብስ ሚሳይል ሲተኮስበት የሚያሳይ ያሉትን የቪዲዮ ምስል ትላንት ረቡዕ አውጥተዋል፡፡ እአአ በዚህ በግንቦት ወር ብቻ ተመትቶ ተጥሏል የተባለ ሦስተኛ የዩናይትድ ስቴትስ ሰው አልባ አውሮፕላን መሆኑ ነው፡፡

የደሕንነት ጉዳይ ላይ ስለሚናገሩ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚንስቴር ባለስልጣን ለአሶሲየትድ ፕሬስ በሰጡት ቃል “የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ዕዝ የእንቅስቃሴ ስልጣን ክልል ውስጥ የአየር ኅይላችን አንድም አውሮፕላን አልወደቀበትም" ብለዋል፡፡

ዝርዝር ውስጥ ገብተው ለማብራራት ግን ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የማዕከላዊ ደህንነት ድርጅት ሲአይኤ ሪፐር የተባሉትን ድሮኖች በየመን የአየር ክልል አሰማርቶ እንደሚያውቅ የሚታመን ሲሆን በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ እንዳልሆነ አሶሥየትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG