ዋሺንግተን ዲሲ —
የሪፑብሊካን ፓርቲው እጩ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትላንት ማታ ከዲሞክራቷ ሂለሪ ክሊንተን ጋር ባደረጉት ሦስተኛውና የመጨረሻው ክርክር ላይ፥ የምርጫውን ውጤት ለመቀበል ቃል አልገባም ብለዋል።
ሁለቱ የዋይት ሃውስ ቤተ መንግሥት ተስፈኞች ላስቬጋስ ኔቫዳ ባደረጉት በትላንቱ ክርክራቸው ወቅት በተጨማሪ፥ ሩሲያን፥ ፍልሰተኞችንና ለዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በሚሰየሙት ዳኛ አመራረጥ ላይ ተጋጭተዋል።
ባልደረባችን ጄም ማሎኒ ከዋሺንግተን የአንድ ሰዓት ተኩሉን ውይይት ጨምቆ አዘጋጅቶታል።
የደጋፊዎች አስተያየቶችም ታክሎበታ፤ ሰሎሞን ክፍሌ ያቀርበዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡