በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሄራዊ ብክለትን የመቆጣጠር ቀን በጭስ በታፈነችው ደልሂ ተከበረ


ፎቶ ፋይል፦ ኒው ደልሂ፤ ህንድ
ፎቶ ፋይል፦ ኒው ደልሂ፤ ህንድ

ህንድ ምንም እንኳ የሀገሪቱ ዋና ከተማ ኒው ደልሂ ሰማይ በጭስ ደመና የተዋጠ እና የአየር ጥራት መጠቆሚያ መስፈርቱም አገሪቱ ያለችበት እጅግ ከወረዱት ደረጃ መሆኗን የሚያሳይ ቢሆንም፣ ዛሬ ብሄራዊ ብክለትን የመቆጣጠር ቀን አክብራ ውላለች፡፡

በዋና ከተማዋ ኒው ደልሂ ብስክሌት የሚጠቀሙት ሀርኪራት ሲንግ መናን የተባሉት ነዋሪ ለመተንፈስ ከባድ ችግር እየፈጠረብኝ ነው፡፡” ይላሉ፡፡

“ለበርካታ ዓመታት ብስክሌት ነድቻለሁ፡፡ በደልሂ ዛሬ ያለው ብክለት እጅግ የሚያሳዝን ነው፡፡ ከዚህ በፊት ካለሁበት እስከ መዳረሻዬ ድረስ ከ15 እስከ 20 ደቂቃዎች የሚወስድብኝ መንገድ ዛሬ ከ40 እና 45 ደቂቃዎች በላይ ይወስድብኛል፡፡ በጣም የሚያበሳጭ መሆኑን እያየነው ነው፡፡ ለመተንፈስ ራሱ ከባድ ችግር ፈጥሮብኛል፡፡” ብለዋል ነዋሪው፡፡

በየዓመቱ የሚከበረው የደቡብ እስያ ብሄራዊ የብክለት ቁጥጥር ቀን በማዕከላዊ የአገሪቱ ክፍል እአአ በ1984 ከአንድ ጸረ ተባይ ኬሚካል ድንገት አምልጦ በወጣው የቦሆፓል ጋዝ ቢያንስ 3ሺ500 ሰዎች ከሞቱበት እለት ጋር የተገጣጠመ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ደልሂ በዓለም እጅግ ከተከበሉ ከተሞች መካከል አንዷ ናት፡፡

20 ሚሊዮን ነዋሪዋችዋ በአብዛኞቹ የክረምት ቀናት ከተሽከርካሪ በሚወጣ ጭስ ብክለት፣ ከኮንስትራክሽን ግንባታዎች በሚቦን አቧራ፣ ከአጎራባች ግዛቶች በሚቃጠሉ የሰብል ገለባዎች ጭስ የተነሳ እጅግ የሚጎዱ መሆኑን የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG