በዓለም የታወቁት የፊዚክስ ሊቅ ስቲቭን ሃውኪንግ በ76 ዓመት ዕድሜያችው ዛሬ አረፉ። ዓለም ከተጀመርበት ጊዜ አንስቶ ጨረርም ሆነ ሌላ ነገር ሾልኮ ሊወጣ የማይችልበት መስክ ውስብስብነት ድረስ የሚሄድ የጠፈር ጥናትና ምርምር አድርገዋል።
ለአሥርት ዓመታት ያክል በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ በሂሳብ ፕሮፌሰርነት አግልግለዋል። ዛሬ ታድያ ካምብሪጅ ከተማ በሚገኘው ቤታችው በሰላም እንዳረፉ የቤተሰባቸው ቃል አቀባይ አስታውቀዋል።
የሃውኪንግ ልጆች ሉሲ፣ ሮበርትና ቲም ባወጡት መግለጫ ትልቅ የሳይንስ ሊቅና ልዩ ሰው ነበሩ። ሥራቸውና ያስተላለፉት ቅርስ ለዓመታተ ሲታወሱ ይኖራሉ ብለዋል።
ሃውኪንግ በ21 ዓመት ዕድሚያቸው በያዛቸው በሽታ ምክንያት መናገር አይችሉም ነበር። መንቀሳቀስ ስለማይችሉም በተንቀሳቃሽ ወንበር ላይ ሆነው ነበር የሚዘዋወሩት። የሚናገሩትም ከተንቀሳቃሻ ወንበራቸው ጋር በተያያዘ የድምፅ መሳርያ በኩል ነበር።
ሀኪሞች የጥቂት ዓመታት ዕድሜ ብቻ እንደሚኖቸው ነበር የነገሯው። ሆኖም እስካሁን በነበረው ጊዜ ከመኖር አልፈው የትልቅ ጥናትና ምርምር ቅርስ ትተው ለማለፍ ችለዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ