በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፀረ ኮሮናቫይረስ ግብረሃይል


የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚንዳንት ማይክ ፔንስ
የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚንዳንት ማይክ ፔንስ

ዋይት ኃውስ የፀረ ኮሮናቫይረስ ግብረሃይሉን ከአንድ ወር ገደማ በኋላ ሊዘጋ ማቀዱን ተሰማ። በሃገሪቱ በየቀኑ በቫይረሱ የሚጠቃው ሰው ከ20ሺህ በላይ ለህልፈት የሚዳረገውም፤ በቀን ከ1ሺህ እስከ 2ሺህ እንደሚደርስ እየተገለጸ ባለበት በአሁን ወቅት ነው።

አስተዳደሩ ወረርሽኙን የሚመለከቱ ሥራዎች ሃገርቀፍ አመራሩ ከዚህ የአውሮፓውያን ግንቦት ወር መጨረሻ፣ አለበለዚያም ሰኔ መጀመሪያ ላይ ከግብረሃይሉ ወደ ፌዴራል መንግሥቱ መሥሪያ ቤቶች ለማዛወር እያቀደ መሆኑን፣ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ማይክ ፔንስ አስታውቀዋል።

ይህ እንደ ሃገር ለወረርሽኙ በምንሰጠው ምላሽ ምን ያህል ትልቅ ዕርምጃ እንደተጓዝን የሚንፀባርቅ ነው ብለዋል።

XS
SM
MD
LG