በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ሞዛምቢክ ጉብኝት ላይ ናቸው


ፎቶ ፋይል፦ በተመድ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደ ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ
ፎቶ ፋይል፦ በተመድ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደ ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ

በሦስት የአፍሪካ ሀገሮች ጉብኝት ላይ ያሉት በተመድ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደ ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ሞዛምቢክን በመጎብኘት ላይ ናቸው፡፡

አምባሳደር ግሪንፊልድ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የዩናይትድ ስቴትስን እና የአፍሪካን ትስስር በእጅጉ ለማጎልበት ካላቸው ዕቅድ በተያያዘ አፍሪካን የጎበኙ ሁለተኛ ከፍተኛ ባለሥልጣን ናቸው፡፡

የገንዘብ ሚንስትሯ ጃነት ዬለን ካለፈው ሳምንት ጀምረው ለአስር ቀናት ሴኔጋልን ዛምቢያን እና ደቡብ አፍሪካን ጎብኝተዋል፡፡

አምባሳደር ግሪንፊልድ በሞዛምቢክ ጉብኝታቸውን ዛፍ በመትከል እና ከበጎ ፈቃደኞች ጋር ሆነው የባህር ዳርቻ አካባቢን በማጽዳት ጀምረዋል፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ በተለይ በተፈጥሮ አካባቢ እና በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳዮች ከሞዛምቢክ ጋር በአጋርነት ለምታከናውነው ሥራ ትልቅ ቦታ የምትሰጠው መሆኗን አጥብቀው አስገንዝበዋል፡፡

በሞዛምቢክ ቆይታቸው ከተመድ ባለሥልጣናት ከሥራ ፈጣሪዎች ከዩናይትድ ስቴትስ የልውውጥ ፕሮግራም ተሳታፊዎች እንዲሁም በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ ከሚሰሩ የሲቪል ማኅበረሰብ አባላት ጋር እንደሚወያዩ ተገልጿል፡፡

አምባሳደር ግሪንፊልድ ከሞዛምቢክ በኋላ ወደ ኬኒያ ይጓዛሉ፡፡

XS
SM
MD
LG