በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ ለሱዳንና ለአካባቢው አገሮች ተጨማሪ 245ሚ. ዶላር ርዳታ መደበች


የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስተር አንተኒ ብሊንከን
የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስተር አንተኒ ብሊንከን

የአሜሪካ መንግሥት፣ በሱዳንና በአካባቢው አገሮች ያሉ ሕዝቦች ለገጠማቸው ሰብአዊ ቀውስ የሚውል፣ የ245 ሚሊዮን ዶላር ርዳታ፣ ባለፈው ሳምንት እንደ መደበ፣ የአገሪቱ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ ዛሬ በአወጡት የጽሑፍ መግለጫ አስታውቀዋል።

ከአጠቃላይ ርዳታው 143 ሚሊዮን ዶላሩ፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ሥር ካለው የሥነ ሕዝብ፣ የፍልሰት እና የስደተኖች ጉዳይ ቢሮ የሚገኝ ሲኾን፣ 103 ሚሊዮን ዶላሩ ደግሞ፣ ከአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ተቋም(USAID) የሰብዓዊ ርዳታ ቢሮ እንደሚገኝ፣ ብሊንከን አስታውቀዋል።

“በድጋፍ ገንዘቡ፣ የሰብአዊ ረድኤት አጋሮቻችን፣ በመካሔድ ላይ ያለው ግጭት በአገር ውስጥ ያፈናቀላቸውን 840ሺሕ ሰዎችንና ወደ ጎረቤት ሀገራት የሸሹትን 250ሺሕ ሰዎችን ለመርዳት ያውሉታል፤” ብለዋል ብሊንከን በመግለጫቸው።

ዐዲሱን ርዳታ ጨምሮ፣ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት፣ ለሱዳንና ለጎረቤት አገሮች የተሰጠው ገንዘብ 880 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል።

አሜሪካ፣ ለአፍሪካ ቀንድ ትልቁ ለጋሽ አገር መኾኗን ያወሱት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣ በጦርነቱ ምክንያት በአገር ውስጥ ለተፈናቀሉትና ለሌሎችም ሰብአዊ ድጋፋቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

XS
SM
MD
LG