በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ ለዩክሬን ተጨማሪ እርዳታ ጠየቀ


ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋኒ ዱያሪች
ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋኒ ዱያሪች

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለዩክሬን ቀውስ ሰብአዊ እርዳታ የሚውል ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ መጠየቁን አሶሲየትድ ፕሬስ ዘገበ።

የሚያስፈልገው የገንዘብ ድጋፍ ከ2.25 ወደ 4.3 ቢሊዮን ዶላር ማደጉን የዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ ቃል አቀባይ ስቴፋኒ ዱያሪች ኒው ዮርክ ውስጥ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ከዩክሬን ህዝብ ከሩብ በላይ የሚሆነው በመጭዎቹ አራት ወራት ውስጥ ሰብአዊ እርዳታ እንደሚፈልግ ቃል አቀባዩ አክለው ገልጸዋል።

ጦርነቱ በተጀመረባቸው የመጀመሪያዎቹ አምስት ወራት ውስጥ ቢያንስ 2.3 ሚሊዮን የሚሆኑ ዩክሬናዊያን የጥሬ ገንዘብ እንደተደረገላቸው ቃል አቀባዩ መናገራቸውን የዜና አውታሩ ዘግቧል።

በመጭው የሰሜን ንፍቀ ክበብ ክረምት ወራት የሙቀት መጠበቂያ፣ ማብሰያና መንቀሳቀሻ ጋዝ፣ ሌላ ነዳጅና መብራት የማግኘት ዕድላቸው አነስተኛ የሆኑ ብዙ ሰዎች እንደሚፈናቀሉ ዱያሪች የተነበዩት ዱያሪች እነሱን መርዳት ቅድሚያ የሚሰጡት ጉዳይ መሆኑን አመልክተዋል።

XS
SM
MD
LG