አዲስ አበባ —
“የእርስዎ ተራ ነው” በሚል ርዕስ በአፍሪካ ብልጽግናን ማረጋገጥ በሚቻልበት ጉዳይ ላይ በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን መሪነት ውይይት ተካሂዷል።
በውይይቱ ላይ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ረዳት ዋና ፀሀፊ እና የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ፀሃፊ ቬራ ሶን ግዌ፣ የዓለም ንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ንጎዚ ኦኮንጆ እና በተባበሩት መንግስታት የአሜሪካ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ ተሳታፊ ነበሩ፡፡
በበይነ መረብ የተካሔደው ውይይቱ በዋናነት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ የተጎዳው የአፍሪካ ኢኮኖሚ እንዲያገግም እና በአህጉሪቱ በዘላቂነት ብልጽግናን ለማረጋገጥ ምን መደረግ አለበት በሚሉ ሐሳቦች ላይ ያተኮረ ነው።
የኮቪድ-19 ወረርሽኝን መቆጣጠር እና ኢንቨስትመንትን ማሳደግ ደግሞ ትኩረት የተሰጡባቸው ነጥቦች ናቸው፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።