በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ ዋና ጸሀፊ ወደ ኦሎምፒክ ከማምራታቸው በፊት ስለ ኢትዮጵያ ተናገሩ


ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሀፊ አንተኒዮ ጎተሬዥ
ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሀፊ አንተኒዮ ጎተሬዥ

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሀፊ አንተኒዮ ጎተሬዥ "የኢትዮጵያ ህዝብ እየተካሄደ ባለው ግጭት ከፍተኛ የደም መፋሰስ ውስጥ ይገኛል" በማለት ይህ ሊያበቃ እንደሚገባ መጭውን የክረምት ኦሎሞፒክ ምክንያት በማድረግ ዛሬ ባስተላለፉት መልዕክት አስገነዘቡ፡፡

ዋና ጸሀፊው ወደ ኦሎምፒኩ ስፍራ ከማምራታቸው በፊት ባስተላለፉት መልዕክታቸው

"ለብዙ ሺህ ዓመታት በኦሎምፒክ ጨዋታዎች በሚደረጉበት ቦታ ሁሉ፣ በየትም ቦታ ያሉ፣ ሁሉም ወገኖች፣ ግጭቶችንና ጥላቻን እንዲያቆሙ መጠየቅ የኖረ ልማድ" መሆኑን ጠቅሰዋል ብለዋል፡፡

አስክተለውም "እኔም ለክረምት ኦሊምፒክ ለመጓዝ በምዘጋጅበት በዚህ ጊዜ በኢትዮጵያ ላሉ ወገኖች ሁሉ ጦርነቱ በአስቸኳይ እንዲቆያም ጠንከር ያለ ጥሪዬን አቀርባለሁ።" ብለዋል፡፡

"ይህ ደግሞ ውጤታማ የሰብአዊ እርዳታ ተደራሽነት እንዲደርስ በማድረ በመላው ኢትዮጵያ ለተጎዱ ህዝቦች ሁሉ እፎይታን ያስገኛል፡፡" ያሉት ዋና ጸሀፊው

"እነዚህ እርምጃዎችም ሁሉንም ኢትዮጵያውያንን ያሳተፈ አስፈላጊው ሀገራዊ ውይይት እንዲደረግ መንገዱን በመክፈት ይረዳሉ" ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ዋና ጸሀፊው በመጨረሻው

"አሁንም ለሁሉም ተሳታፊ ወገኖች መልካም በሆነው የኦሎምፒክ ወግና መንፈስ መሰረት ልዩነቶቻቸውን አስወግደው ህይወትና ለማዳን ወደ እውነተኛው ሰላም የሚወስደውን መንገድ እንዲይዙ ጥሪዬን በድጋሚ አስተላልፋለሁ" ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG