በ2024ቱ ምርጫ ዶናልድ ትረምፕ ሕዝባዊውንም ኾነ ኢሌክቶራል ካሌጅ ተብለው የሚጠሩትን የአስመራጮች ድምፅ አሸንፈው ዛሬ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።
ትረምፕን ለድል ያበቋቸው በርካታ ጉዳዮችና ሁኔታዎች እንዳሉ የፖለቲካ ተንታኞችም ሆነ የትረምፕ ደጋፊዎቻቸው ያስረዳሉሉ።
ትረምፕ ከዚህ በፊት ባልተለመደ ሁኔታ በ34 ወንጀሎች ጥፋተኝዐ ቢባሉም ለድል በቅተዋል። አሜሪካውያን በኢኮኖሚውም ሆነ በሌሎች ሁኔታዎች የገጠማቸውን ችግር እንድሚረዱ እና ችግሩንም ለመቅረፍ እንደሚሰሩ ቃል መግባታቸው የድምጽ ሰጪዎችና ደጋፊዎቻቸው ጆሮ መድረሱ፣ “አሜሪካ ትቅደም” የሚለውና ጠንከር ያለ ነው የተባለው መልዕክታቸው፣ ቁልፍ የሆኑ ድምጽ ሰጪዎችን ኢላማ አድርገው መልዕክታቸውን ማስተላለፋቸው፣ ኢኮኖሚው በፈጠረው ሁኔታ ኑሮ የከበዳቸውን ድምጽ ሰጪዎችን ኢላማ ማድረጋቸውም ተጠቃሽ ነው።
ትረምፕ ለድል የበቁበት መንገድ ምን ይመስላል? በምንስ ይግለጻል? ለድል የበቁባቻው ሌሎች ምክንያቶችስ ምንድን ናቸው ስንል በቴክሳስ ካሊንስ ኮሌጅ የኢኮኖሚክስ መምህር የሆኑትን ፕሮፌሰር ሞሃመድ ጣሂሮን ጋብዘናል።
ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም