ወጣት የምርምር እና የሥነ ጽሁፍ ሰው ነው። በጀርመኑ የድሬስደን የቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የኮምፒውተር ምሕንድስና ተባባሪ ፕሮፌሰር ተማራማሪ እና የኢንርጂ ቤተሙከራ ኃላፊም ነው።
በሳይንስ እና ምርምር፣ በፍልስፍና እና እንዲሁም በጽነ ጽሁፉ ዓለም ገናና ዕውቅና ያላቸውን የአራት ቀደምት ጠቢባን፡- ዕውቁን የፊዚክስ ሊቅ የአልበርት አንስታይንን፤ ሕቡዉን የአንጎል ክፍል በሚያጠናው የሥነ ልቦና ምርምር ዘርፍ መሥራችትነት የሚታወቀውን የሲግመንድ ፍሮይድን፣ የገናናውን ደራሲ ጋዜጠኛ እና ፈላስፋ የቴዎዶር ዶስቶየቭስኪን እና እንዲሁም የሌላውን እውቅ ብዕረኛ የሊዮ ቶልስቶይን የሕይወት ፍልስፍናዎች የሚመረምረውን The Reason For Life የተሰኘ መጽሃፉን ጨምሮ .. ምርምር እና ጥናት በሚያደግበት የሞያ መስክና እንዲሁም በልቦለዱ ዓለም በርከት ያሉ መጻሕፍት ጽፏል።
ዋልተንጉስ ዳርጌ ይባላል።
በተከታዩ ምጥን ወጋችን ከዶ/ር ዋልተንጉስ ዳርጌ እና ሥራዎቹ ጋር እናስተዋውቃችሁ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ