በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፊሊፒንሱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የቀድሞው አምባገነን ልጅ እየመሩ ነው


ድምፅ ለመስጠት ወረፋ ሲጠባበቁ ማኒላ፣ ፊሊፒንስ እአአ ግንቦት 9/2022
ድምፅ ለመስጠት ወረፋ ሲጠባበቁ ማኒላ፣ ፊሊፒንስ እአአ ግንቦት 9/2022

በፊሊፒንስ ትናንት ሰኞ በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከሥልጣናቸው የተወገዱት የቀድሞ አምባገነን የፈርዲናንድ ማርኮስ ልጅ በትልቅ የድምፅ ብልጫ እየመሩ መሆኑን ይፋዊ ያልሆኑ ቆጠራዎች አመለከቱ።

ከሰባ ሰባት ከመቶ የሚበልጠው የመራጭ ድምፅ ተቆጥሮ ማርኮስ ሃያ አምስት ሚሊዮን ድምፅ ያገኙ ሲሆን የቅርብ ተፎካካሪያቸው የሰብዓዊ መብት ተሟጋቿ እና የአሁኗ ምክትል ፕሬዚዳንት ሌኒ ሮብሬዶ አስራ ሁለት ሚሊዮን ገደማ አግኝተዋል።

ቀጣዩ የፊሊፒንስ ፕሬዚዳንት ተሰናባቹን ፕሬዚዳንት ኤዱዋርዶ ዱቴርቴን በፀረ ሱስ አስያዥ መድሃኒቶች ዘመቻቸው በብዙ ሺዎች የተቆጠሩ ሰዎች ላይ በፈጸሙት ግድያ ለፍርድ እንዲያቀርብ በህዝቡ መጠየቁ አይቀርም ተብሏል።

የአንዲት ከተማ ከንቲባ የሆኑት የዱቴርቴ ሴት ልጅ ሳራ ዱቴርቴ የማርኮስ ምክትል ፕሬዚዳንት ለመሆን ተወዳድረዋል።

XS
SM
MD
LG