አዲስ አበባ —
አምስተኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌደሬሽን ምክር ቤት ሦስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን የጋራ መክፈቻ ስብሰባ ዛሬ ተካሂዷል፡፡
የጋራ ስብሰባውን በንግግር የከፈቱት ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ በአለፈው ዓመት የአሥር ነጥብ ዘጠኝ በመቶ እድገት መመዝገቡን ተናግረዋል፡፡
ሁለቱ ምክር ቤቶች የዚህን ዓመት የሥራ ዘመን የጀመሩት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አባ ዱላ ገመዳ በዚህ ኃላፊነት ለመቀጠል ፍላጎት እንደሌላቸው በይፋ ባሳወቁበት ማግስት ነው፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ