ዋሽንግተን ዲሲ —
በቅርቡ ከዚህ በዓለም በሞት የተለዩንን አንጋፋ እና ዕውቁን ገጣሚ፣ የፎክሎር አዋቂ እና መምህር ሰይፉ መታፈሪያ ፍሬውን ሕይወት እና ሥራ ለመዘከር የተሰናዳ ቅንብር ነው።
በ1964 የጻፏትን የመጀመሪያቸው ዐፈር ያነሣ ሥጋ የተሰኘች መጽሃፋቸውን ጨምሮ ውስጠት፣ የተስፋ እግር ብረት ግጥሞች፣ የተጉዋጎጠ ልብ እንዲሁም በስደት የጻፏቸው ከራስ ድምበር ባሻገር፣ ዐባይ ፈንጂ የቀበረ ውኀ’ን ጨምሮ ስድስት የግጥም መጻህፍት ለንባብ አብቅተዋል። በዝርው ከተጻፉ መጻሕፍቶቻቸው “ኮፌ-ሰንዳፋ-ኮልፌ” እና “ሀሁ በአሜሪካ” ይገኙባቸዋል። የበርካታ ቋንቋዎች አዋቂም ናቸው።
ለመሆኑ ሰይፉ መታፈሪያ ማናቸው? ምን ዓይነት ሰው ነበሩ?
ታናሽ ወንድማቸው ብርጋድዬር ጀነራል መስፍን ኃይሌ እና ከቀድሞ ተማሪዎቻቸው አንዱ የነበሩት በጀርመን የሃምቡርግ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ እና ኢትዮጵያ ጥናቶች የትምህርት ክፍል የፎክሎር መምህር ዶ/ር ጌቴ ገላዬ እንዲህ ያስታውሷቸዋል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።