በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቋንቋዎች የስነ ጽሁፍ እና የሥነ መለኮት ሊቁ ማስታወሻዎች


ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ
ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ

በተለይ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር የነበራቸው ቆይታ። የጥንታዊ ጽሁፎች፣ የፎክሎር፣ የታሪክ እና የሥነ መለኮት ሊቅ የግዕዝ ቋንቋ ቀዳሚ ተማራማሪም ነበሩ - ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ። 

እውቁና አንጋፋው የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አዋቂው ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ባለፈው ሃሙስ ነው በ90 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት።

ከአምስት መቶ በላይ የግዕዝ መጻህፍት መዘርዝር አሰናድተዋል። የኢትዮጵያን ጥንታዊ መዛግብትና መጻህፍት አጥንተዋል። ባሕረ ሃሳብ፤ ደቂቀ አስጢፋኖስ፡ የአባ ባህሪይ ድርሰቶች (ትርጉም) እና ሌሎች በተለያዩ ርዕሰ-ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮሩ ከሃያ በላይ የጥናት እና የምርምር መጻህፍት ጽፈዋል።

ከ1950 እስከ 1960ዎቹ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሴማዊ ቋንቋ ጥናት፣ በአማርኛ እና ግዕዝ ሥነ-ጹሑፍ እንዲሁም ሰዋሰው በመምህርነት አገልግለዋል። በህይወት ዘመናቸው ላበረከቷቸው ታላላቅ ሥራዎችም ከተለያዩ ዓለም አቀፍ እና የኢትዮጵያውያን ተቋማት በርካታ ሽልማቶችን ተቀብለዋል።

እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ1987ዓም ለኦርየንታል ጽሁፎች ጥናት እና ምርምር ላበረከቱት አስተዋጽኦ ለብሪቲሽ አካዳሚ አባልነት ሲመረጡ፤ የላቀ ሥራ ላበረከቱ ግለሰቦችና ተቋማት እና ድጋፍ ዕውቅና የሚሰጠው የሥመ-ጥሩን የመካርተር ፋውንዴሽን ሽልማት ተቀሉ። እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ1995ዓም በዩናይትድ ስቴትሱ የኢትዮጵያውያን የሽልማት ድርጅት ማኅበረ ግዩራን ዘረ-ኢትዮጵያ ከዓመቱ ተሸላሚዎች አንዱ ሆኑ። በኢትዮጵያ ጥናቶች እና በሴማዊ ቋንቋዎች ምርምር በሚታወቁት እንግሊዛዊው ምሁር ኤድዋርድ ኡለንዶርፍ ስም የተሰየመውና በዚሁ መስክ ከፍተኛ የምርምር ሥራዎችን ላበረከቱ ምሁራን የሚሰጥ ሜዳሊያም ተሸልመዋል።

ፕሮፌሰር ጌታቸው በህመም ላይ ሳሉ በተለያዩ ቀናት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ካደረግናቸው ቃለ ምልልሶች በመጠኑ እንጋብዛችሁ።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

የቋንቋዎች የስነ ጽሁፍ እና የሥነ መለኮት ሊቁ ማስታወሻዎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:16:29 0:00


XS
SM
MD
LG