የቀድሞው የታይላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር የታክሲን ሺንዋትራ ቀንደኛ ደጋፊ የሆኑ ሰውዬ፣ የአንድ የሌላ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ስም በማጥፋት ተከሰው ቀሪ ሕይወታቸውን ወህኒ ቤት ሊያሳልፉ መሆናቸው ተሰማ።
በስም ማጥፋት የተወነጀሉትና ወህኒ የሚወርዱት ጃቱፖርን ፕሮምፓን በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቢሂስት ቪጃጂቫ እአአ በ2010 የተቃውሞ ሰልፍ በተካሄደበት ወቅት ባንኮክ ላይ ንግግር ሲያደርጉ፣ "ነፍሰ-ገዳይ" ብለው በመናገራቸው ነው ክስ የተመሰረተባቸው።
እናም የታይላንዱ ጠቅላይ ፍንርድ ቤት፣ ጃቱፓርን ጥፋተኛ ብሎ በይኖባቸዋል።
ቀደም ብሎ ችሎት የተካሄደባቸው ሁለት የበታች ፍርድ ቤቶች ግን ክሱን ውድቅ አድርገውት እንደነበርም ተገልጧል፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ