በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፖለቲካ አለመረጋጋት በሚስተዋልባት ኢትዮጵያ የሀገረ-ብሄር ግንባታ እውን ሊሆን ይችላል?


ፕሮፌሰር ካሳሁን ብርሀኑ፣ ዶ/ር ኦይቪድ ኦድላንድና፣ ዶ/ር ዘነበ በየነ
ፕሮፌሰር ካሳሁን ብርሀኑ፣ ዶ/ር ኦይቪድ ኦድላንድና፣ ዶ/ር ዘነበ በየነ

ከቅርብ አመታት ወዲህ ኢትዮጵያ የፓለቲካ አለመረጋጋት፣ ግጭቶች፣ የእርስ በእርስ የጥልቻ ንግግሮች ተደጋግመውና መልካቸውን እየቀየሩ የሚረብሿት አገር ሆናለች። የዝነኛው የኦርሚኛ ድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ተከትሎም፣ በኦሮሚያ ክልል እና በአዲስ አበባ የጠፋው የሰው ሕይወት፣የጎደለው የሰው አካልና የጠፋው ንብረት ለዚህ ማሳያ ነው። ይህ አለመረጋጋት ደግሞ በኢትዮጵያ የንግድና ምጣኔ ሀብት ሥርዓት ላይ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ተፅኖ እያሳረፈ ነው።

የዛሬ ሁለት አመት ‘ለዚህ ችግር ዋና መንስኤው የኢትዮጵያ መንግስታት ከሀገረ-ብሄር ግንባታ ይልቅ ለመንግስት ግንባታ ትኩረት ሲሰጡ በመኖራቸው ነው’ የሚሉ ምሁራን ተሰባስበው የሀገረ-ብሄር ግንባታ ፕሮጀክት ግብረ-ሀይል በማቋቋም፣ 2010 ላይ ሁለት ሲምፖዚየሞችን አካሂደው ነበር።

በነዚህ ሲምፖዚየሞች ላይ ወደ 15 የሚሆኑ ምሁራን፣ ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ችግር ለማውጣት የሀገር- ብሄር ግንባታ አስፈላጊነትና፣ የጋራ ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠር በሚቻልባቸው ሀሳቦች ዙሪያ የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎችን አቅርበው ነበር።

ይህን መነሻ አድርገን በፖለቲካ አለመረጋጋት በስፋት በሚስተዋልባት ኢትዮጵያ የሀገረ-ብሄር ግንባታ እውን ሊሆን ይችላል?’ በሚል ርዕስ የሲምፖዚየሙ አዘጋጆች የነበሩትን ሶስት ምሁራን በእንግድነት ጋብዘናል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

የፖለቲካ አለመረጋጋት በሚስተዋልባት ኢትዮጵያ የሀገረ-ብሄር ግንባታ እውን ሊሆን ይችላል?
please wait

No media source currently available

0:00 0:32:49 0:00


XS
SM
MD
LG