በኢትዮጵያ ህገወጥ ነጋዴዎችና ደላሎች ሸማቹን ማኅበረሰብ ለተባባሰው የኑሮ ውድነት ዳርገውታል ሲሉ የሸማች መብት ተቆርቋሪ ማኅበራትና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ይከሳሉ፡፡
ነጋዴዎች በበኩላቸው "መንግሥት ግብርን ጨምሮ ሕጋዊ ነጋዴው ላይ የሚያደርሰው ጫና በርትቷል" ሲሉ ቅሬታቸውን ያሰማሉ፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የንግድ ሥራ ትምህርት ቤት መምህር የሆኑት ዶክተር ዳኪቶ አለሙ ደግሞ ለተፈጠረው የዋጋ ንረት አንዱ ምክንያት የዘመነ የንግድ ሥርዓት መፍጠር አለመቻሉ መሆኑን ይናገራሉ፡፡
በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ያለው የሸቀጦች የዋጋ ንረት 19 በመቶ እንደሆነ የሚገልጸው መንግሥት በበኩሉ "የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት እየሠራሁ ነው" ሲል ይገልጻል፡፡
መድረክ / ፎረም