በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ጦርነት ተከትሎ የሃውቲ ታጣቂዎች በቀይ ባህርና አካባቢው ላይ በመርከቦች ላይ የሚያደርሱት ጥቃት መጨመሩ ኢትዮጵያን ጨምሮ የአፍሪካ ቀንድ ሃገራትን ደህንነት ስጋት ውስጥ የጣለ መሆኑን ምሁራን ተናግረዋል:: አለም አቀፍ ማህበረሰብ ትኩረትንም መካከለኛው ምስራቅ ላይ በመሆኑ የሱዳን ጦርነት ጨምሮ አፍሪካ ቀንድ ላይ ያሉ ችግሮች ትኩረት እንዲቀንስ አድርጏል ይላሉ::
ኢትዮጵያን ጨምሮ የቀጠናው ሃገራት ወደ መካከለኛው ምስራቅ ጦርነቶች ተስበው እንዳይገቡም ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸውም መክረዋል::