በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች በመከላከያ ሰራዊት ላይ የተፈፀመውን ጥቃት አወገዙ


“የሃገር ተገንና ከለላ በመሆነው የመከላከያ ሰራዊት ላይ ተፈፀመ የተባለው ጥቃት ለመመከት በሚደረግ ሂደት ውስጥ ወንድም የትግራይ ህዝብ የጦርነቱ ሰለባ እንዳይሆን” ሲሉ የሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ። በመከላከያ ሰራዊት ላይ የተፈፀመው ጥቃት አውግዘዋል።

የሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ከሲዳማ ክልል ፕሬዚዳንት እና ከፌዴራል ባለሥልጣናት ጋር በወቅታዊ የሃገር ጉዳይ በተወያዩበት ወቅት፣ የኢትዮጵያን ህዝብ ለ27 ዓመታት በዝብዟል ባሉት በህወሓት ቡድን ላይ መንግሥት እየወሰደ ያለው እርምጃ ብዘገይም እንደሚደግፉትና በመንግሥት ጎን እንደሚቆሙ ገልፀዋል።

የሲዳማ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ዳስታ ለዳሞ ህዝቡ አካባቢውን ነቅቶ እንዲጠብቅ አሳስበው፣ በክልሉ ከተማና ወረዳ ቀበሌያት ለህዝብ ደኅነንት ሲባል አዲስ መታወቂያ እንዲሰጥ መከልከሉንና ሌሎች እገዳዎች መጣሉን ገልፀዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡

የሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች በመከላከያ ሰራዊት ላይ የተፈፀመውን ጥቃት አወገዙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:54 0:00


XS
SM
MD
LG