በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሲዳማ ጉዳይ፡- ውዝግቡ፣ ማንነት ለይተው የተነጣጠሩ ጥቃቶችና ቀጣዩ መንገድ


“..የክልልን ጥያቄ የሚቃወሙ ግለሰቦች ናቸው ባሏቸው እና አልፎ አልፎም ከሌላ አካባቢ መጡ በሚሏቸው ለ’ጀነሬሽን’ በኖሩ ሰዎች ላይ የተፈጸመው እጅግ አሳዛኝ (ድርጊት) ነው። “ አቶ ደጀኔ ወልደ አማኑኤል። “.. ጥያቄው ሰፊ መሠረት ያለው ነው። ነገር ግን የመናበብ ችግር ነው የሚታየኝ።..” አቶ ሽመልስ ኪታንቾ።

የሲዳማ ዞንን የክልልነት ጥያቄ ተከትሎ ካለፈው ሃሙስ አንስቶ በተቀሰስቀሰውና የበርካታ ሰዎች ሕይወት የጠፋባቸውን ግጭቶች፣ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ያለውን የጸጥታ ሁኔታ፣ የግጭቶቹን መንስኤና ዘላቂ መፍትሄዎች አስመልክቶ የተካሄደ ውይይት ነው።

ተወያዮች፡- አቶ ደጀኔ ወልደ አማኑኤል የቀድሞው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ መሥራች አባል የነበሩ .. አቶ ሽመልስ ኪታንቾ ደቡብ ኢትዮጵያ አረንዴ ኮከቦች ሕብረት ሊቀ መንበር እና ዶ/ር ፍስሃ አስፋው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማሕበረሰብ ጥናት ክፍል በመምሕርነት እንዲሁም በቀድሞው የብሔረሰቦች ጥናት ተቋም በባለሞያነት ያገለገሉ ናቸው።

የፖለቲካ ጥያቄዎችን፣ በቡድኖች እና በግለሰቦች አማካኝነት ማንነትን ለይተው በንጹሃን ላይ የተነጣጠሩ ጥቃቶችንና እንዲሁም በወንጀሎቹ የሚጠየቁ ወገኖችን ጉዳይ አስመልክቶ የተነሱ ጥያቄዎችን ይመረምራሉ፤ ቀጣዩንም መንገድ ያመላክታሉ።

የሲዳማ ጉዳይ፡- ውዝግቡ፣ ማንነት ለይተው የተነጣጠሩ ጥቃቶች .. ክፍል አንድ
please wait

No media source currently available

0:00 0:17:41 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG