በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩክሬይን አዲስ ፕሬዚዳንት ለመምረጥ እየተዘጋጀች ነው


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ዩክሬይን፣ ቀደም ብላ ባወጣችው ፕሮግራም መሠረት፣ በመጪው እሑድ አዲስ ፕሬዚዳንት ለመምረጥ እየተዘጋጀች መሆኗ ተገለፀ። ሁለቱ ተፎካካሪዎች ደግሞ ከ2 ሳምንታት በኋላ ድጋሚ ምርጫ ያደርጋሉ።

የምርጫው አሸናፊ፣ በምሥራቅ በኩል በሩስያ ከሚታገዙት ሽምቅ ተዋጊዎች ጋር ከሚካሄደው ጦርነት በተጨማሪ፣ አገሪቱ ካለባት ሙስና እንዲሁም ደካማ ኢኮኖሚ ጋር በመጋፈጥ ቀላል የማይባል ሥራ እንደሚጠብቀው ከወዲሁ ታውቋል።

ለውድድሩ 39 ዕጩዎች የተመዘገቡ ቢሆንም፣ በወቅቱ ፕሬዚዳንት ፔትሮ ፖሮሼንኮ፣ በታዋቂው የፖለቲካ ሰው ዩሊያ ታይሞሼንኮ እና በታዋቂው የቴሌቪዥን ኮሜዲያን ቮሎዳይሜር ዜሌኒስኪ መካከል የሚካሄደው ፉክክር ለሦስት ሳምንታት የሚዘልቅ እንደሆነ ነው የተገመተው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG