በሰሜን ጎንደር ዞንዳባት ወረዳ በምትገኝ “ጭና ተክለሀይማኖት” በተባለች የገጠር ቀበሌ ውስጥ ከ200 በላይ ንፁሀን ዜጎች በህወሓት ታጣቂዎች መገደላቸውን መንግሥት፣ ተጎጂዎችና የዓይን እማኝ መሆናቸውን የገለፁ ነዋሪዎች ተናገሩ።
“የህወሓት ታጣቂዎች በቀበሌዋ በቆዩባቸው አምስት ቀናት ውስጥ ንፁሃን ሰዎችን ቤትለቤት እየዞሩ ገድለዋል።” ሲሉ የዐይን እማኝ መሆናቸውን የገለፁ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ሮይተር እና አሶሽዬትድ የትግራይሀይሎች ብለው በጠሯቸውና የኢትዮጵያ መንግሥት “አሸባሪ ህወሓት” ብሎ የሚጠራቸው የህወሓት ታጣቂዎች ባለፉት ቀናት ያጋጠማቸውን ሽንፈት ተከትሎ ከ120 በላይ ንፁሃን ዜጎችን መግደላቸውን የአካባቢውን ባለስልጣናት ጠቅሰው ዘግበዋል። ግድያው ባለፉት 10 ወራት በተካሄደው ጦርነት እጅግአ ሰቃቂ ጭፍጨፋ መሆኑንም አሶስዬት ድፕሬስ ገልጿል።
የህወሓቱ ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በዛሬው ዕለት በትዊተር አማካኝነት ባስተላለፉት መልዕክት የተባለውን ውንጀላ አልፈጸምንም ሲሉ አስተባብለዋል።
በሌላ ዜና በዳባት ወረዳ በምትገኘው የጭና ቀበሌ ከፈተኛ ቁጥር ያለው አስከሬን በትናንትናው ዕለት መገኘቱ በእጅጉ አዋኪ ሁኔታ መከሰቱን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮምሽን በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ አመለከተ። መግለጫው አክሎም የተገደሉትን ሰዎችን ቁጥር እና ማንነት የማጣራት ሥራ መቀጠላቸውን ጠቅሶ ከጥቃቱ የተረፉ ወገኖች ግን የተገደሉት ሲቪሎች መሆናቸውን መናገራቸውን ዘግቧል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮምሽን አያይዞም በክልሉ ከሚያደርገው የሰብዓዊ መብት ምርመራ ጋር በተያያዘ ወደ ዳባት እና ሌሎች በነዋሪዎች ላይ ጉዳት የደረሰባቸው አካባቢዎች መርማሪዎች የሚልክ መሆኑን በዘገባው አስታውቋል።
ባህርዳር የምትገኘው ዘጋቢያችን ተጎጂዎችን እና የአካባቢውን ባለሥልጣናት አነጋግራ ያጠናከረችውን ዘገባ ከሮይተርስ እና ከአሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ ጋር በማጣመር አቅርባዋለች።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡