በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

‘በስንቱ’ በአሜሪካ


ዕውቁ ተዋናይ ዓለማየሁ ታደሰ፣ አሉላ ከበደ
ዕውቁ ተዋናይ ዓለማየሁ ታደሰ፣ አሉላ ከበደ

ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ውስጥ በተጫወታቸው ቁጥራቸው የበዛ ሥራዎቹ እና ላቅ ያለ አድናቆት ባተረፈለት አጨዋወቱ በኢትዮጵያ የቴአትር እና የሲኒማ መድረክ ይበልጥ ከሚታወቁ ምርጥ ተዋናዮች አንዱ ለመሆን በቅቷል። በዚህም በርካታ ሽልማቶችን ተቀብሏል፤ ዕውቁ ተዋናይ ዓለማየሁ ታደሰ።

ዕውቁ ተዋናይ ዓለማየሁ ታደሰ
ዕውቁ ተዋናይ ዓለማየሁ ታደሰ

በተከታታዩ የቴሌቭዥን ድራማ በሚጫወተው የመሪ ተዋናይ ገጸ ባህሪ ስም የሚጠራው እና በአሁኑ ወቅት በሃገር ውስጥና በውጭ ሃገራት ባሉ ተመልካቾች በዩቲዩብ በስፋት በመታየት ላይ ያለው ‘በስንቱ’ ከአዲስ የኪናዊ ሥራው አድናቂ ተመልካቾች ጋር አስተዋውቆታል። ስለበስንቱ’ እና በአሁኑ ወቅት በዩቱብ በመታየት ላይ ስላለው አጋፋሪ ስለተሰኘው ሌላ ድራማው፣ ስለ ተውኔት፣ ስለ ሲኒማ እና ስለሞያዊ ህይወቱ፣ እንዲሁም በህይወቱ የሚከተለውን የኑሮ ፍልስፍና እና ትርጓሜ ያጫውተናል።

በዩናይትድ ስቴትስ ቆይታው በተለይ ከሞያው ጋር በተዛመደ የማየት እድል ከገጠሙት መድረኮችም አንዳንዱን እናነሳሳለን። ሁሉንም በአሜሪካ ድምጽ ስቱዲዮ ከአሉላ ከበደ ጋር ካደረገው ዘለግ ያለ ውይይት ተከታታሉ።

 ‘በስንቱ’ በአሜሪካ
please wait

No media source currently available

0:00 0:28:10 0:00

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG