በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኖቤል ኮሚቴው ጠ/ሚ ዐቢይ ጦርነቱን የማስቆም የተለየ ኃላፊነት አለባቸው አለ


ፎቶ ፋይል፦ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ
ፎቶ ፋይል፦ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

የኖሮዌይ ኖቤል ኮሚቴ ዛሬ ሀሙስ ባወጣው መግለጫ እኤአ በ2019 የኖቤል ሽልማቱን የተቀዳጁት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሰሜን ኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ የሚገኘውን ጦርነት የማስቆም የተለየ ኃላፊነት አለባቸው ሲል አስታወቀ፡፡

የኮሚቴው ሊቀመንበር ቤርት ሬስ አንደርሰን ለአጃንሳ ፍራንስ ፕሬስ በሰጡት መግለጫ በጠቅላይ ሚኒስትርነታቸውም ሆነ እንደ ሰላም ኖቤል አሸናፊነታቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጦርነቱን የማስቆም የተለየ ኃያላፊነት አለባቸው ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በወቅቱ የኖቤል ሽልማት የተቀበሉበት በጀመሩት የሰላም ተነሳሽነት፣ ከኤርትራ ጋራ ባደረጉት የሰላም ሥምምነትና ለሁለገብ የፖለቲካ ዴሞክራሲ የልማትና የሰብአዊ መብቶች ተነሳሽነት መሆኑን ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG