በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምሥጋና


የምሥጋና ቀን ሠልፍ በፊላደልፊያ
የምሥጋና ቀን ሠልፍ በፊላደልፊያ

ዛሬ ባሜሪካ የምሥጋና ቀን ነው፡፡

Thanksgiving Day ይባላል በእንግሊዝኛው አጠራር፡፡ አሜሪካዊያን በዚህ ዕለተ በየዓመቱ እቤታቸው ከቤተሰባቸው ጋር ሆነው በረከታቸውን ያስባሉ፤ ምሥጋና ያቀርባሉ፤ ይበላሉ፣ ይጠጣሉ፣ ይደሰታሉ፡፡

የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ደግሞ ከወትሮው ለየት ያለ፣ በሕገመንግሥቱ ያልተጣፈ፤ በልማድ ቢጎድል ምናልባት ቅር የሚል ግን አንድ ኃላፊነት አለበት፡፡ ለአውዳመቱ ለእርድ ከተዘጋጁት እርኩሞች ለአንዷ የምህረት በረከቱን ያወርድላታል፡፡ ባራክ ኦባማም ይህንኑ ኃላፊነታቸውን ትናንት ተወጥተዋል፡፡

በነገራችን ላይ የበዓሉ ፍሪዳ እርኩም ነች፡፡

ለመሆኑ ይህ የምሥጋና ቀን መነሻው ምንድነው? ለዘንድሮውስ እንዴት ይሆን አሜሪካዊያኑ ሲዘጋጁለት የሰነበቱት?

ዴብራ ብሎክ ከፍሎሪዳ፣ አራሽ አራባሳዲ ከሜሪላንድ፣ ኬንት ክሌይን ከዋይት ኃውስ የዘገቧቸውንና ሌሎችም መረጃዎችን አካትቶ ሰሎሞን አባተ ያቀናበረውን የታንክስጊቪንግ ዘገባ ያዳምጡ፡፡

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG