በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሚያንማር በኢንተርኔት በሚያጭበረብሩ ማዕከላት ተገደው ይሠሩ የነበሩ ቻይናውያን ወደ ሀገራቸው በመመለስ ላይ ናቸው


በሚያንማር በኢንተርኔት በሚያጭበረብሩ ማዕከላት ተገደው ይሠሩ የነበሩ የቻይና ዜጎችን አሳፍሮ እንደሚጓዝ የሚታመን አውቶቡስ በታይላንድ ታክ ግዛት እአአ የካቲት 20 ቀን 2025
በሚያንማር በኢንተርኔት በሚያጭበረብሩ ማዕከላት ተገደው ይሠሩ የነበሩ የቻይና ዜጎችን አሳፍሮ እንደሚጓዝ የሚታመን አውቶቡስ በታይላንድ ታክ ግዛት እአአ የካቲት 20 ቀን 2025

በምሥራቅ ሚያንማር በኢንተርኔት አማካይነት ማጭበርበር በሚፈጽሙ ማዕከላት በግዴታ ሲሠሩ የነበሩ 1ሺሕ የሚሆኑ ቻይናውያንን ወደ ሀገራቸው የመመለሱ ሂደት ተጀምሯል።

ሠራተኞቹ ወደ ታይላንድ ድንበር ከተወሠዱ በኋላ ወደ ቻይና በሚያቀና የቻርተር በረራ እንዲወሰዱ በመደረግ ላይ ነው።

ባለ ሁለት ወለል ሁለት አውሮፕላኖች የመጀመሪያው ዙር ተመላሾችን ምዕራብ ታይላንድ ድንበር ላይ ወደምትገኝ ከተማ ወስደዋል።

ከታይላንድ ጋራ የሚያዋስነውን ድንበር የሚቆጣጠረውና ከሚያንማር ሁንታ ጋራ ተባባሪ የሆነው የድንበር ጥበቃ ኅይል፣ 10 ሺሕ የሚሆኑና በኮምፒውተር የማጭበርበር ወንጀል ይፈጽማሉ ከተባሉ ማዕከላት ጋራ ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሰዎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተመልክቷል።

በወንጀላኛ ቡድኖች ቁጥጥር ሥር ባሉ ማዕከላት የሚገኙት የውጪ ዜጎች በኢንተርኔት አማካይነት በመላው ዓለም የማጭበርበር ሥራ እንዲሠሩ መገደዳቸውን ተናግረዋል። አብዛኞቹም ከፍተኛ ክፍያ የሚያስገኝ ሥራ ታገኛላችሁ ተብለው ተታለው እንደሄዱ ተናግረዋል።

ባለፈው ሳምንት ታይላንድ 260 የሕገ ወጥ አዘዋዋሪ ቡድኖች ሰለባዎችን ከሚያንማር ተቀብላለች፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ተገልጿል፡፡ የታይላንድ ጦር ባለፈው ሳምንት በሰጠው ቃል፣ ቁጥጥር በማይደረግበት በሁለቱ ሀገሮች ድንበር አቅራቢያ በሚገኙ የሳይበር ወንጀል ማዕከሎች ላይ ዘመቻ የከፈተችው ሚያንማር ሠራተኞቹን ወደመጡበት ሀገራት እየመለሰች መሆኑ ተገልጿል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG