በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኦፕራ ዊንፍሬ በዘንድሮው የምርጥ-ምርጥ የቴሌቭዥንና የሲኒማ ሥራዎች ሽልማት ጎልደን ግሎብ


Oprah Winfrey poses in the press room with the Cecil B. DeMille Award at the 75th annual Golden Globe Awards
Oprah Winfrey poses in the press room with the Cecil B. DeMille Award at the 75th annual Golden Globe Awards
ኦፕራ በዘንድሮው የምርጥ-ምርጥ የቴሌቭዥንና የሲኒማ ሥራዎች ሽልማት ጎልደን ግሎብ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:32 0:00

በቀይ ምንጣፍ ላይ የተንጣለለ የጥቁር ባሕር ተመስሏል።

በሆሊውድ እና በመላዋ አገሪቱ በተለያዩ የሥራ ቦታዎች በሴቶች ላይ የሚፈጸመውን ሥር የሰደደ ወሲባዊ ወከባ ለመፋለም ለሚንቀሳቀሰውን ታይም ኢዝ አፕ የተባለውን የመብት ተሟጋች ቡድን በመደገፍ ጥቁር የለበሱ በሥነ ሥርዓቱ የተገኙ ሴቶች የለበሱት ልብስ የከሰተው ገጽታ ነው።

በቴሌቭዥን እና በሲኒማው መስክ ባለፈው ዓመት የተሰሩ ምርጥ ሥራዎችን የሚዘክረው የሆሊውዱ የውጭ ፕሬስ ማኅበር የሚያሰናዳውና እንደ ወትሮው ሁሉ ለየት ባለ ጉጉት የተስተናገደው የትላንቱ የጎልደን ግሎብ ሥነ ሥርዓት፤ ሆሊውድ በሴቶች ላይ በሚፈጸሙት እና ለዓመታት በዘለቁት የወሲባዊ ወከባ ጥቃቶች ቅሌት ከተናጠች ወዲህ የመጀመሪያው መሆኑ ነው።

የኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ባለፈው የጥቅምት ወር አስገድዶ የመድፈር ጥቃትን ጨምሮ በያኔው ገናና እና ከፍተኛ ተሰሚነት የነበረው የፊልም አቀናባሪ ሃርቬይ ዋይንስቲን “ተፈጽመዋል” በተባሉ ለአሥርት ዓመታት የዘለቁ፤ ወሲባዊ ወከባዎች ውንጀላ ያተተ ዝርዝር ዘገባ ተከትሎ፤ ሌሎች በርካታ ገናናዎችንና አይደፈሬዎችን ያንበረከኩ ያልተጠበቁ ድምጾች፤ ክሶችና ስሞታዎች በየቀኑ ይዥጎድጎዱ ጀመር።

በትላንቱም ጎልደን ግሎብ የሥነ ሥርዓቱ አስተናጋጅ፤ ታዋቂ የምሽት የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢ እና ኮሜዲያን ሲት ማየር ይሄንኑ የወሲባዊ ቅሌት ሥሜት ባዘሉ የሰሉ ሥላቆች የምሽቱን መድረክ መጋረጃ እንዲህ ሲል ከፈተ።

“በዚህ ክፍል ውስጥ የሌለውን ግዙፍ ጉዳይ የማስተዋወቂያው ሠዓት ይመስለኛል።ሃርቬይ ዋይንስቲን በዛሬው ምሽት ከዚህ የለም። እንደ ሰማሁት ጭምጭምታ ከሆነ እብድና አብረውት መሥራት የሚቻል ሰው አይደለም። ሃሳብ አይግባችሁ ከአንድ ሃያ ዓመታት በኋላ ተመልሶ ይመጣል። በሕልፈታቸው መታሰቢያ በታዳሚው ጩኰት ከመድረኩ እንዲወርዱ በመጠየቅ የመጀመሪያው ሰው ይሆናሉ። እንዲያ ነው የሚመስለው ነገሩ።”

እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ከ1914 እስከ 1958 በነበረው ጊዜ ውስጥ ከ70 በላይ ፊልሞችን በሰራውና የአሜሪካ የፊልም አባት በሚል ቁልምጫ በሚታወቀው ዕውቁ የፊልም ዲሬክተር እና አቀናባሪ ሴሲሊ ቢ ዴሚሌ ሥም የተሰየመውን ለዕድሜ ልክ ሥራዎች የሚሰጥ ሽልማት የዘንድሮ ተሸላሚ የፊልም ተዋናይዋ አቀናባሪና የቴሌቭዥን ሠው ኦፕራ ዊንፍሬ ሽልማቱን በተቀበለችበት ወቅት ያሰማችውም ንግግር አዳራሹን ከዳር እስከ ዳር ያቀጣጠጠለ ነበር።

ኦፕራ በዚያ የብዙዎችን ቀልብ በልዩ ሥሜት በናጠ ንግግሯ ከሰባ ዓመታት በፊት በነጭ አሜሪካውን ወረበሎች በቡድን የተደፈረች አንዲት ጥቁር አሜሪካዊት አስታወሰች።

“እነኚያ ሬሲ ቴይለር’ን ሊያጠፉ የሞከሩ ሰዎች በሕግ ሳይጠየቁ ቀርተዋል። ሬሲ ቴይለር ዘጠና ስምንተኛውን የልደት በዓሏን ለማክበር ጥቂት ሲቀራት ከአሥር ቀናት በፊት ነው ያረፈችው። አይደፈሬ ነገር ግን ርሕራሄ በሌላቸው ወንዶች በተደፈረ ባሕል ውስጥ አያሌ ዓመታት ኖራ አለፈች።

በእነኚያ አይጠየቄ ጉልቤ ወንዶች የደረሰባቸውን ጥቃት ለመናገር የደፈሩ ቁጥራቸው የበዛ ሴቶችም ሰሚ ሳይኖራቸው ለረዥም ዘመናት ዘለቁ። ዛሬ ግን ያ ሰዓት ያበቃ ይመስላል።

የእነኚያ ጉልበተኞች ጊዜ አለፈ። አዎን! አለፈ።” ብላለች።

በርካታ እንስት ተዋናዮች ከሴቶች መብት ተሟጋቾችና የዘር ልዩነትን በመቃወም የፍትሕ ጥሪ ለማሰማት ከተሰለፉ ብዙዎች ጋር በመሆን ነው።

አነጋጋሪውና ቀልብ ሳቢያ የኦፕራ ንግግራ የመጪዋ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የመሆን ዕቅድ መጀመሪያ አድርገውም ወስደውታል። ይህን አስመልክቶ በኦፕራ በኩል የተባለ ነገር በሌለበት በእርግጥ የሚሆነው ወደፊት ይሆናል የሚታወቀው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG