ዩናይትድ ስቴትስ ቴክሳስ ክፍለ ሃገር አንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተኩስ ከፍቶ ሃይ ሥድስት ሰው ገድሎ ሌሎች ከሃያ በላይ ያቆሰለው የሃይ ስድስት ዓመት ዕድሜው ዴቪን ኪሊ ጥቃቱን ለመፈጸም ምን እንዳነሳሳው የቴክሳስ ባልሥልጣናት ክትትል ይዘዋል።
ከዩናይትድ ስቴትስ የአየር ኃይል በባህሪ ጉድለት የተባረረ ሰው መሆኑ ተገልጿል። የቴክሳስ ሀገረ ገዢ ግሬግ አበት ለሲቢኤስ ቴሌቭዥን በሰጡት ቃል የኃይለኝነት ዝንባሌ እና ችግር የነበረው ሰው እንደነበር ግልፅ ነው፣ ጊዜ ጠብቆ እንደሚፈነዳ ፈንጂ ነበር ብለዋል። ትናናት ረፋዱ ላይ ጥቃቱን ያደረሰው ኬሊ ከቤተ
ክርስቲያኑ ጋር ግንኙነት የነበረው ይመስላል ብለዋል አገረ ገዢው።
አማቾቹ ትናንት አልነበሩም እንጂ አልፈው አልፈው እዚያ ቤተክርስቲያን እንደሚያስቀድሱ ሀገረ ገዢው ጠቅሰው ይሄ የሚያሳየው ግለሰቡ ያገኘው ቦታ የከፈተው ጥቃት እንዳልሆነ ነው ብለዋል። በዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስቴር መረጃዎች መሰረት እኤአ ከ 2010 እስከ 2012 በአየር ኃይል ውስጥ አገልግለዋል በ2012 ሚስቱንና ልጁን በመደብደብ አንድ ዓመት እሥራት ተፈርዶበት በኋላ ከጦር ኃይሉ እንዲሰናበት መደረጉ ተገልጿል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ