በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቴክሳስ በሺዎች የሚቆጠሩ ህገወጥ ድንበር ተሻጋሪዎችን ብታስርም ቁጥሩ አልቀነሰም


 ፎቶ ፋይል፦ ፍልሰተኞች በዩናይትድ ስቴትስ በኤል ፓሶ፣ ቴክሳስ ድንበር ጠረፍ ላይ መጓጓዣ እየተጠባበቁ እ አ አ ግ ንቦት 10/2023
ፎቶ ፋይል፦ ፍልሰተኞች በዩናይትድ ስቴትስ በኤል ፓሶ፣ ቴክሳስ ድንበር ጠረፍ ላይ መጓጓዣ እየተጠባበቁ እ አ አ ግ ንቦት 10/2023

በዩናይትድ ስቴትስ የቴክሳስ ግዛት እኤአ ከ2021 ጀምሮ በሜክሲኮ ድንበር በኩል ጥሰው ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ 10ሺ የሚጠጉ ፍልሰተኞችን በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ፡፡

ስደተኞቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በአገረ ገዥው ግሬግ አቦት 10 ቢሊዮን ዶላር በፈጀውና “ሎን ስታር” ተብሎ በሚጠራው ዘመቻ አካል በሆነው ፕሮጀክት መሆኑን አሶሴይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

ቴክሳስ ውስጥ ከመጭው መጋቢት ጀምሮ ፖሊስ ህገ ወጥ ፍልሰተኞችን ከመንገድ ላይ በቁጥጥር ስር እንዲያውልና ለዳኞችም ከአገር የማባረር ሥልጣን የሚሰጥ አዲስ ደንብ ወጥቷል፡፡

የዜጎች መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች እነዚህ እርምጃዎች ህገ መንግስታዊ ያልሆኑ እና የፌዴራል መንግስትን በስደተኝነት ላይ ያለውን ስልጣን የሚጥሱ ናቸው ሲሉ ይከራከራሉ።

አዳዲስ ደንቦች እየወጡና የጠበቁ ቁጥጥሮች ተግባራዊ እየተደረጉ ቢሆንም በሜክሲኮ ድንበር በኩል ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የሚገቡ ህገ ወጥ ስደተኞች ቁጥር ከወትሮው እጅግ እየጨመረ መምጣቱ ተመልክቷል፡፡

እኤአ በ2021 1.2 ሚሊዮን የነበረው ህወ ገጥ ፍልስተኞቹ ቁጥር ወደ 1.5 ሚሊዮን ከፍ ማለቱ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡

በህገወጥ ፍልስተኞቹ ዙሪያ ለመምከር የዩናይትድ ስቴትስ እና የሜክሲኮ ባለሥልጣናት ትናንት ረቡዕ ሜክሲኮ ሲቲ ውስጥ ተገናኝተው ተወያተዋል፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG