ዋሺንግተን ዲሲ —
ሁለት የሮይተርስ ጋዜጠኞች፣ የሚያንማር ውስጥ “ምስጢራዊ ሰነዶች ይዘዋል” ተብለው ስለተጠረጠሩ በቁጥጥር ሥር ዋሉ።
“ሰነዶቹ በአሁኑ ወቅት እዚያው አገር ከምያንማር ራክሂነ ውስጥ ካለው የፍልሰተኞች ቀውስ ጋር የተገናኙ ናቸው” ብሏል መንግሥቱ ዛሬ ረቡዕ በሰጠው መግለጫ።
በቁጥጥር ሥር የዋሉት የሮይተርስ ጋዜጠኞች፣ “ስለ ራክሂነ የደኅንነት ኃይሎች የሚገልፁ መረጃዎችን ለውጪ አገር ዜና አውታሮች ለማስተላለፍ ሞክረዋል» ሲሉ፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት ተናግረዋል።
በቀድሞዋ በርማ በዛሬው ሚያንማርውስጥ ያለው የዩናይትስ ስቴትስ ኤምባሲ በሰጠው መግለጫ፥ “የጋዜጠኞቹ መታሰር አሳስቦናል” ብሎ ሲያበቃ፣ “ዴሞክራሲ ዕውን ይሆን ዘንድ ጋዜጠኞች ሥራቸውን በነፃነት ማከናወን መቻል አለባቸው” ብሏል።፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ