በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደሴ ላይ ይገነባል ለተባለው ሆስፒታል ከሕዝብ ተሰብስቦ ገቢ አልተደረገም የተባለ ገንዘብ ክርክር አስነሳ


ደሴ ከተማ
ደሴ ከተማ

ደሴ ከተማ ላይ ሊገነባ ለታቀደው፣ “ወሎ ተርሸሪ ኬር የልእለ ህክምናና ትምህርት ማዕከል” ግንባታ ከሕዝብ የተሰበሰበው ገንዘብ በአግባቡ ገቢ እንዳልተደረገ የፌደራል ዋና ኦዲተር አስታወቀ። ኦዲተር መሥሪያ ቤቱ ባቀረበው ሪፖርት፣ የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱን ተጠያቂ አድርጓል።

ደሴ ላይ ይገነባል ለተባለው ሆስፒታል ከሕዝብ ተሰብስቦ ገቢ አልተደረገም የተባለ ገንዘብ ክርክር አስነሳ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:54 0:00

የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ በበኩላቸው፣ ለፕሮጀክቱ ገቢ ማሰባሰቢያ እንዲኾን በሚል የርዳታ ገንዘብ ለማሰባሰቢያ የተበተኑት ኩፖኖችና የሎተሪ ትኬቶችን መልሶ ለመሰብሰብ የተለያዩ ችግሮች ስላጋጠሟቸው ገንዘቡን መሰብሰብ እንዳልቻሉ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።

በውዝግቡ ዙሪያ የተጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG