በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሽብር ክሥ ችሎት ሦስተኛ ቀን ውሎ


ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የተከሰሰባቸው ስብሰባዎችና መጣጥፎች ሁሉ ሕጋዊና ለሰላም የቆሙ ናቸው ሲል ቃሉን ሰጥቷል፡፡ መንግሥት አስቀድሞም ማስጠንቀቂያ ሰጥቶት እንደነበር ለችሎቱ አስታውሷል፡፡

አምስተኛ ተከሣሽ ክንፈሚካኤል ደበበ በአንደኛ ተከሣሽ በአቶ አንዱዓለም አራጌ

በችሎቱ ላይ ተገኝቶ የነበረው ሌላው ዘጋቢያችን ፒተር ሃይንላይን ባጠናቀረው ሌላ ዘገባ ደግሞ እስክንድር ነጋ ለችሎቱ ባሰማው ቃል “የሕሊና እሥረኛ ነኝ” ማለቱንና መንግሥትን በኃይል ለመጣል አሲረሃል ተብሎ የቀረበበትን ክሥ ማስተባበሉን፤ የፍርድ ቤቱን ብይን አስመልክቶም ታሪክ እንደሚፈርድ ማሳሰቡን አመልክቷል፡፡

እስክንድር ለሃያ ደቂቃ ያህል ለችሎቱ በሰጠው ቃል እንደዐረብ አብዮት ዓይነት ንቅናቄ ኢትዮጵያ ውስጥም መሠረት ሊኖረው እንደሚችል መፃፉንና ለሰላማዊ ትግል መጥራቱን ያመነው እስክንድር ለሁከት ወይም ሕገመንግሥቱን በኃልይ ለመጣል ለሚያነሣሣ አድራጎት አለመቀስቀሱን ተናግሯል፡፡

በዚሁ የችሎቱ የመጀመሪያ ዕለት የቀረቡት የመጀመሪያው ተከሣሽ አቶ አንዱዓለም አራጌ ክሦቹ ሁሉ የተመሠረቱት በሃሰት ላይ ተመርኩዘው መሆኑን መናገራቸው ተዘግቧል፡፡

በችሎቱ ላይ ዋና ምስክር ሆነው የቀረቡት የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳ ተከላካዮቹ የፖለቲካ ለውጥ እንዲመጣ ይንቀሣቀሱ የነበሩት በሕጋዊ መንገድ እንደነበረ ተናግረዋል፡፡

ተከላካዮቹ “የሽብር አድራጎት ለመጠንሰስ ያሴሩ ነበር” ሲል አቃቤ ሕግ ቀደም ሲል እንደማስረጃ ያቀረበባቸው የተቀረፁ ድምፆች የተጫጫሩና ለመስማት አዳጋች የሆኑ የስልክ ንግግር ቅጂዎች እንደነበሩ ፒተር በዘባው ላይ ጠቁሟል፡፡

የሰብዓዊ መብቶችና ሃሣብን የመግለፅ ነፃነት ተሟጋች ቡድኖች የኢትዮጵያውን ፀረ-ሽብር ሕግ የሃገሪቱን ሕገመንግሥት የሚረግጥና የፖለቲካ ነፃነትን የሚያግድ ነው ሲሉ አንደሚነቅፉት ይታወቃል፡፡

እስክንድርም በቁጥጥር ሥር ከመዋሉ በፊት ሕጉ ተቃውሞን ለመገደብ የታሰበ ነው ሲል በኢንተርኔት ባወጣው ፅሁፍ ተችቶት ነበር፡፡

የ1997ቱን ምርጫ ተከትሎ ከእስክንድር ጋር ታሥራ የነበረችው ባለቤቱ ሰርካለም ፋሲል ዛሬ ለቪኦኤ በሰጠችው ቃል እስክንድር “የግንቦት ሰባት አባል ነህ” መባሉ እንደሚያሣዝነውና የሚናገረው የግንቦት ሰባት አባል አለመሆኑንና ጋዜጠኛ መሆኑን እንደሆነ አመልክታለች፡፡

እስክንድርና አቶ አንዱዓለም ከ1997ቱ ምርጫ በኋላ ከታሠሩና በኋላም በምህረት ከተለቀቁ 130 ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ሰዎች መካከል ይገኙ ነበር፡፡

ባለፈው መስከረም አዲሱ ፀረ-ሽብር ሕግ ተግባራዊ እንደሆነ ከሌሎች ስድስት ተከሣሾች ጋር በቁጥጥር ሥር መዋላቸውና አብዛኞቻቸው ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚኖሩ ሌሎች 18 ሰዎች የግንቦት ሰባት ደጋፊዎች ናችሁ ተብለው በሌሉበት መከሰሳቸው ይታወቃል፡፡

የአሁኖቹ ተከሣሾች ጥፋተኛ ናቸው ተብሎ ከተበየነ የሞት ፍርድ ሊጠብቃቸው እንደሚችል የሕግ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG