በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፓኪስታን ፍ/ቤት በአንድ ክርቲያን ሴት ላይ የቀረበውን ክስ ሰረዘ


አሲያ ቢቢ
አሲያ ቢቢ

የፓኪስታን ከፍተኛ ፍ/ቤት በአንድ ክርቲያን ሴት ላይ የቀረበውን የሃይማኖት ማጥለም ክስ ሰርዟል።

የፓኪስታን ከፍተኛ ፍ/ቤት በአንድ ክርስቲያን ሴት ላይ የቀረበውን የሃይማኖት ማጥለም ክስ ሰርዟል። ክሱ በፓኪስታን ህግ መሰረት በሞት ያስቀጣል። እንዲህ አይነቱ ያልተለመደ ብይን የአከራሪ ሙስሊሞች ተቃውሞ አከተሏል። ግጭት እንዳይነሳም ስጋት አሳድሯል።

“በአሲያ ቢቢ ላይ የቀረበው ክስ የማያጠራጥር ማስረጃ አልቀረበበትም” ይላል ፍርዱ።

“የሰማሁትን ማመን አቅቶኛል። አሁን ልወጣ እችላልሁ ማለት ነው? እውነት እንድወጣ ይፈቅዱልኛል?” ስትል ለዘጠኝ አመታት ያህል በእስር የቆየቸው ተከሳሽ ለፈረንሳይ የዜና አገልግሎት ተናግራለች።

በርካታ እስላማውያን ፓርቲዎች ብይኑን አልተቀበሉም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG