በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮሎራዶ ግዛት በምግብ መደብር ውስጥ በተከፈተ ተኩስ 10 ሰዎች ተገደሉ


ዩናይትድ ስቴትስ ኮሎራዶ ክፍለ ግዛት ቦልደር ከተማ የምግብ እና ሸቀጣ ሸቀጥ መደብር ውስጥ በተከፈተ ተኩስ 10 ሰዎች ተገደሉ።
ዩናይትድ ስቴትስ ኮሎራዶ ክፍለ ግዛት ቦልደር ከተማ የምግብ እና ሸቀጣ ሸቀጥ መደብር ውስጥ በተከፈተ ተኩስ 10 ሰዎች ተገደሉ።

ትናንት ምሽት ዩናይትድ ስቴትስ ኮሎራዶ ክፍለ ግዛት ቦልደር ከተማ በሚገኝ የምግብ እና ሸቀጣ ሸቀጥ መደብር ውስጥ በተተኮሰ ጥይት አስር ሰው መገደሉን ፖሊስ አስታወቀ።

የቦልደር ከተማ ፖሊስ አዛዥማሪስ ሄሮልድ ትናንት ማታ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል ከተገደሉት ሰዎች መካከል አንደኛው በመደብሩ ጥይት የሚተኩስ ሰው አለ የሚሉ ሪፖርቶች በመጡበት ጊዜ መጀመሪያ በስፍራው የደረሰው ፖሊስ ኤሪክ ታሊ መሆኑን ገልጸዋል። የጀግንነት ተግባር ፈጽሞ ያለፈ ሲሉም ሙቿን ፖሊስ አወድሰውታል።

ጥቃቱን በመፈጸመ የተጠረጠረ አንድ ሰው በቁጥጥር ስር መዋሉን የገለጹት የፖልሲ አዛዡ ምርመራው ቢያንስ አምስት ቀን ሊወስድ ይችላል ብለዋል።

የቦልደር የወረዳ አቃቤ ህጉ ማይክል ዶርቲ የጥቃቱ ምክንያት ይህ ነው ብሎ ቸኩሎ በግምት መናገር እንደማይቻል ገልጸዋል፥ አያይዘውም "እንደወትሮአቸው ምግብ ሊገዙ ከቤታቸው የወጡ ሰዎች፣ አሁን በቁጥጥር ስር በዋለው አጥቂ እጅ ህይወታቸው ተቀጥፏል፤ ለዚህ ጥቃት ሰለባዎችና ለኮሎራዶ ህዝብ ፍትህ እንደሚሰጥ ቃል እገባላችኋለሁ" ብለዋል።

የጥቃቱን ሰለባዎች የመለየቱ እና ቤተሰቦቻቸውን የማርዳቱ ሂደት መቀጠሉን ባለሥልጣናቱ በትናንቱ ጋዜጣዊ መግለጫቸው አስታውቀዋል።

XS
SM
MD
LG