በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶማልያው ግጭት 10 ሰዎች ተገደሉ 15 ቆሰሉ


ሶማልያ ውስጥ በማዕከላዊ የአገሪቱ ክፍል በሚገኙ ሚሊሺያዎች መካከል ትናትን ማክሰኞ በተነሳ የእርስ በርስ ግጭት ቢያንስ 10 ሰዎች መገደላቸውና 15 ሰዎች መቁሰላቸው ተገለጸ፡፡

ግጭቱ የተነሳው ጋላዱድ በተሰኘው ክፍለ ግዛት ባላንባል አውራጃ ውስጥ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ባለሥልጣናት፣ የአካባቢው ማኅበረሰብና የዐይን እማኞች እንደገለጹት በግጭቱ የተሳተፉ ሁለቱም ወገኖች የሮኬት ቦምቦችን ጸረ አውሮፕላን መሳሪያዎችና ጠመንጃዎችን መጠቀማቸውን ተናግረዋል፡፡

ግጭቱ የተከሰተው የሶማሌ ባለሥልጣናት እና ዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች በድርቅና በመሳሰሉ ቀውሶች 245ሺ ሰዎች መፈናቀላቸውን በገለጹበት ወቅት መሆኑም ተመልክቷል፡፡

በተለይ ድርቁ ከቀጠለ ይህ ቁጥር በቅርብ ጊዜ ውስጥ ወደ 1.4 ሚሊዮን ሊያድግ እንደሚችል ተነግሯል፡፡

XS
SM
MD
LG