ሶሪያ ውስጥ በምሥራቅ የአገሪቱ ክፍል በኢራን በሚደገፉ አንጃዎች ላይ በተካሄደ ተከታታይ የድሮን ጥቃት አሥር ሰዎች መገደላቸው ተነገረ።
ዛሬ፤ ሰኞ በተካሄደው የድሮን ጥቃት ከተገደሉት ሦስት ሰዎች መካከል አፍቃሬ ኢራን የሆኑ አንድ ወታደራዊ መሪ እንደሚገኙበት መሠረቱን እንግሊዝ ያደረገው የሶሪያ ሰብአዊ መብቶች ቃፊር ቡድን አስታውቋል።
በድሮን ጥቃቱ የተገደሉ ሌሎች ሰዎችንም አስመልክቶ ክትትል እያደረገ መሆኑን ቡድኑ ጨምሮ ገልጿል።
በኢራን ይታገዛል የተባለው ቡድን አዛዥም ሆኑ ከርሳቸው ጋር የተገደሉት ሁለት ባልደረቦቻቸው የሶሪያ ዜጎች አለመሆናቸውን የመብቶች ቃፊሩ ቡድኑ አመልክቷል።
ኢራን በሶሪያው የእርስ በርስ ጦርነት የታጠቁ አንጃዎችን ማሠማራትን ጨምሮ ደማስቆ ለሚገኘው አጋሯ ወታደራዊ እርዳታ እንደምትሰጥ አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገባ ዘግቧል።
ለድሮን ጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ አንድም አገር ባይኖርም እስራኤል ቀደም ሲልም ዩናይትድ ስቴትስ ጦር በንቃት በሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች ባሉ በኢራን የሚደገፉ ቡድኖችና በሶሪያ መንግሥት ኃይሎች ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ የሚሳይልና የአየር ድብደባዎች ማካሄዷ ተዘግቧል።