በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታሣሪ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጎብኚ ተከለከለ


በኢትዮጵያ በእሥር ላይ የሚገኘውን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
በኢትዮጵያ በእሥር ላይ የሚገኘውን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

በኢትዮጵያ በእሥር ላይ የሚገኘውን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ጤንነት በተመለከተ ባለፈው ሳምንት መዘገባችን ይታወሳል። ዛሬ ባገኘነው መረጃ መሠረት፥ ጋዜጠኛው ያለበት ሁኔታ የእኛን ያሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ ጨምሮ በሌሎችም መገናኛ ብዙሃን ከተገለጸ በኋላ፥ ተመስገን በቤተሰብ እንዳይጎበኝና ስንቅ እንዳይገባለት ተከልክሏል።

ያነጋገርናቸው አንድ የተመስገን ቅርብ የቤተሰብ አባል በአንድ ሳምንት ውስጥ አራቴ ወደ ዝዋይ ሄደው ማየት እንዳልቻሉና ስንቅ ለማስገባትም እንዳልተፈቀደላቸው ሲገልጹ ጠበቃው ችግሩን ለፍርድ ቤት ለማቅረብ እንደሚገደዱ አስረድተዋል።

ሁኔታውን ለማጣራት ዛሬ ወደ ዝዋይ እሥር ቤት ያደረግነው የስልክ ጥሪ ምላሽ አላገኘም። ከዚህ ቀደም ያነጋገርናቸው አንድ ”ስሜ ቢቆይ” ያሉ የማረሚያ ቤቱ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ መሆናቸውን የገለጹልን ሰው ግን፥ “ተመስገን ህክምና ተከልክሏል የተባለው ሀሰት መሆኑን አረጋግጥላችኁለሁ” ብለዋል። ”ጋዜጠኛው በየቀኑ ሃኪም ያየዋል፥ የጤና ችግር የለበትም” ሲሉም አክለዋል።

ዝርዝሩን ሰሎሞን ክፍሌ አቅርቦታል ይህንን የድምፅ ፋይል በመጫን ያዳምጡ።

ታሣሪ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጎብኚ ተከለከለ /ርዝመት -6ደ41ሰ/
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:40 0:00

XS
SM
MD
LG