በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መምህራን ሥራ በማቆማቸው ጠምባሮ ልዩ ወረዳ ትምህርት እንዳልተጀመረ ተገለጸ


መምህራን ሥራ በማቆማቸው ጠምባሮ ልዩ ወረዳ ትምህርት እንዳልተጀመረ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:05 0:00

መምህራን ሥራ በማቆማቸው ጠምባሮ ልዩ ወረዳ ትምህርት እንዳልተጀመረ ተገለጸ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠምባሮ ልዩ ወረዳ፣ ለተከታታይ ሦስት ወራት ደመወዝ ያልተከፈላቸው መምህራን ሥራ እንዳቆሙና የዘመኑ የመማር ማስተማር ሒደትም እስከ አሁን እንዳልተጀመረ፣ መምህራንና ወላጆች ለአሜሪካ ድምፅ በስልክ ተናግረዋል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሓላፊ አቶ አንተነህ በፈቃዱ፣ ችግሩ በሌሎችም አካባቢዎች መኖሩን አምነው፣ በበጀት እጥረት እና በተያያዥ ምክንያቶች የተፈጠረ እንደኾነ ተናግረዋል።

ለመፍትሔውም፣ ከዞኖቹ የሥራ ሓላፊዎች ጋራ እየመከሩ እንደኾነ አስታውቀዋል።

የጣምባሮ ልዩ ወረዳ ወላጆች እና ተማሪዎች ደግሞ፣ በልዩ ወረዳው ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ እንደኾኑና በትምህርታቸውም ወደ ኋላ እየቀሩ ናቸው፤ ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

በሌላ በኩል፣ የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ፕሬዚዳንት ዶር. ዮሐንስ በንቲ፣ ባለፈው ሳምንት ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል፣ መምህራን ለገጠማቸው ችግር፣ መንግሥት አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG