በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቴሌብር ተስፋና ስጋቱ ምንድነው?


የቴሌብር ተስፋና ስጋቱ ምንድነው?

በቅርቡ ኢትዮጵያ ውስጥ በዓይነቱ የመጀመሪያው የሆነው የቴሌብር አገልግሎት ተጀምሯል፡፡ የሞባይል የገንዘብ አገልግሎቱን እንዲሰጥ ከብሄራዊ ባንክ ፈቃድ የተሰጠው የኢትዮ ቴሌኮም የ400 ብሊዮን ብር አጠቃላይ ካፒታል የተፈቀደለት መሆኑም ተመልክቷል፡፡ የስማርት ስልክ ያላቸው ሁሉ የጥሬ ገንዘብ ወይም ቼክ መጻፍ ሳያስፈልጋቸው የተለያዩ የክፍያ አገልግሎቶችን መፈጸም እንዲችሉ ወይም እንዲቀበሉ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የማክሮ ኢኮኖሚስቱ ዶ/ር ኢዮብ ተስፋዬ፣ አገልግሎቱ ከሌሎች አፍሪካ አገሮች አንጻር እጅግ የዘገየ መሆኑን አስታውሰው፣ ባንኮችና የፋይናንስ ሴክተሮችም ለዚህ አገልግሎት ዝግጁ መሆን እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

ቴሌብር በቅርቡ በኢትዮጵያ ቴሌኮም ሥራ ላይ የዋለ አዲስ የክፍያ ሥርዓት ነው፡፡ ገንዘብን በእጅ ስልክ መቀባበል የሚያስችለው ይህ ጥበብ በዓለምና በተለይም በአፍሪካ ትንሽ የሰነበተ ቴክኖሎጂ ቢሆንም በኢትዮጵያ ሥራ ላይ ሲውል ይህ የመጀመሪያው ነው፡፡ አገልግሎቱ የክፍያ ሥርዓቱንና ግብይትን ያቀላጥፋል፣ የባንክ ተጠቃሚ ያልሆኑ በርካታ ሰዎችን ወደ ክፍያ ሥርዓቱ ያመጣል፣ አገሪቱ ለገንዘብ ህትመት የምታወጣውንም ወጭ ይቀንሳል ተብሎለታል፡፡

የማክሮ ኢኮኖሚስቱ ዶ/ር ኢዮብ ተስፋዬም በዚህ ይስማማሉ፡፡ ሊደረጉ ከሚገባቸው ጥንቃቄና ሊወሰዱ ከሚገባቸው ተጨማሪ እምርጃዎች ጋር ቴሌ ብር ለፋይናንሱ ዘርፍ የሚሰጣቸውን ጥቅሞችንና ይዘረዝራሉ፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

የቴሌብር ተስፋና ስጋቱ ምንድነው?
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:03 0:00


XS
SM
MD
LG